የመፈናቀል አደጋ አጋጥሞዎታል? እርዳታ ያግኙ!
Authored By:
Northwest Justice Project
- Read this in:
- Arabic / العربية
- English
- Spanish / Español
- Hindi / हिन्दी
- Cambodian / Khmer
- Korean / 한국어
- Marshallese / Kajin M̧ajeļ
- Mandarin Chinese / 官話
- Punjabi / ਪੰਜਾਬੀ
- Russian / Pусский
- Samoan / Gagana Samoa
- Somali / Soomaali
- Tagalog / Pilipino
- Ukrainian / Українська
- Vietnamese / Tiếng Việt
- Chinese / 中文
ስለ ግዛት እና ፌደራል የማፈናቀል ጊዜያዊ እገዳ እና አከራይዎ በማናቸውም መልኩ ሊያፈናቅልዎ ሙከራ ቢያደርግ ምን ማድረግ እንዳለብዎ በተመለከተ ይወቁ። Facing Eviction? Get Help! (Amharic)
- Contenido
መረጃ
ጊዜያዊ ከቤት ማስወጣት እገዳው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2021 ድረስ ሁሉንም የሚያቆም አይደለም ፣ ግን አብዛኛው መፈናቀልን ያቆማል።
እስከዚህ ጊዜ ድረስ በፌደራል እና የግዛት የማፈናቀል ትዕዛዞች ስር ከ COVID-19-ተያያዥነት ባላቸው ምክንያቶች ኪራይዎን መክፈል ባለመቻልዎ ምክንያት ሊፈናቀሉ አይችሉም።
ያም ሆኖ ወዲያው ሊከሰት የሚችል እና ከፍተኛ የሆነ ለጤና፣ ለደህንነት እና ለንብረት የሚያስጋ ችግር የሚያስከትሉ ከሆነ ሊፈናቀሉ ይችላሉ።
አከራይዎ በተጨማሪም የኪራይ ንብረቱን ለመሸጥ ወይም ወደ ንብረቱ ለመግባት በበመፈለግ ምክንያት ሊያፈናቅልዎ ሙከራ ሊያደርግ ይችላል። የፌደራሉ ጊዜያዊ እገዳ ከዚህ በእጅጉ ይጠብቅዎታል።
- የጊዜያዊ እገዳ መጣል ማለት የኪራይ እዳ የለብዎትም ማለት አይደለም!
- የኪራይ ክፍያ ካልከፈሉ በኋላ ላይ በክፍያዎ ላይ እዳዎን ጨምረው ሊከፍሉ ይችላሉ!
- የቤት ኪራይዎን አሁን የማይከፍሉ ከሆነ ከሰኔ 30 ቀን 2021 በኋላ ሊባረሩ ይችላሉ!
ይህንን ያንብቡ Coronavirus (COVID-19)፥ አከራይዎ በአሁኑ ወቅት እርስዎን ሊያፈናቅል የሚችልባቸው ምክንያቶች ጥቂት ብቻ ናቸው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት።
አከራይዎ ሊያፈናቅልዎ ሙከራ የሚያደርግ ከሆነ ወዲያውኑ የህግ እርዳታ ለማግኘት ይሞክሩ። ካውንቲዎን ከዚህ በታች ይምረጡ፡፡
ሁሉንም የኪራይ ክፍያዎን መክፈል የማይችሉ ከሆነ አከራይዎ አሳማኝ የኪራይ ክፍያ እቅድ ሊያቀርብልዎት ይገባል። የትኛውንም እቅድ ከአከራይዎ በጽሁፍ ያግኙ። ይህንን ያመልከቱ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19)፥ ከአከራዬ ጋር የኪራይ መልሶ ክፍያ እቅድ ውስጥ መግባት ይኖርብኛልን?
መረጃ-ማውረጃን ያውርዱ
- PDF File size: 176.45KB
ተጨማሪ የመረጃ ምንጮች
የሚፈልጉትን ማግኘት አልቻሉም? በዋሽንግተን ግዛት ውስጥ መፈናቀልን ለተመለከቱ ለሁሉም መረጃዎቻችን የእኛን የመፈናቀል ርዕሰ ጉዳይ ዘርፍ ይመልከቱ።