የመፈናቀል አደጋ አጋጥሞዎታል? እርዳታ ያግኙ!

ስለ ግዛት እና ፌደራል የማፈናቀል ጊዜያዊ እገዳ እና አከራይዎ በማናቸውም መልኩ ሊያፈናቅልዎ ሙከራ ቢያደርግ ምን ማድረግ እንዳለብዎ በተመለከተ ይወቁ። Facing Eviction? Get Help! (Amharic) #6311AM

በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የኪራይ ድጋፍ መርሃ ግብሮችን እና ሌላ እርዳታ ያግኙ

 

አሁንም ለኪራይ እርዳታ ማመልከት ይችላሉ!

ተመላሽ የቤት ኪራይ ካለብዎ እና ዝቅተኛ ገቢ ካሎት፣ የቤት ኪራይ እርዳታ አለ። በእርስዎ ካውንቲ ውስጥ የኪራይ እርዳታ እና ሌላ እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶችን ለማግኘት ካውንቲዎን ከዚህ በታች ይምረጡ። *ማስታወሻ፡- የሰሜን ምዕራብ ፍትህ ፕሮጀክት የኪራይ ርዳታን አይሰጥም፣ ነገርግን የተዘረዘሩት ድርጅቶች ይሰጣሉ። 

የኪራይ ድጋፍ ሲባል የዜግነትዎ ወይም የኢሚግሬሽን ሁኔታዎ ምንም ይሁን ምን ሁሉንም ሰው ለመርዳት ነው። ለኪራይ እርዳታ ማመልከት እርስዎ ያስገቡትን ማንኛውንም የኢሚግሬሽን ማመልከቻ አይጎዳም። 

 

ወረዳዎን ይምረጡ፦

[COUNTY DROPDOWN LIST HERE]

አዳዲስ ዜናዎች

የክልሎች እና የፌደራል የማፈናቀል ጥበቃዎች አብቅተዋል። የፌደራል (የበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከላት ወይም CDC) ከቤት ማስወጣት እገዳ ከአሁን በኋላ ለተከራዮች እንደ ከቤት የማስወጣት መከላከያ አይገኝም። የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት CDC በአገር አቀፍ ደረጃ ከቤት ማስወጣት (ለማፈናቀል ለአፍታ ማቆም) ስልጣን የለውም ብሏል። የ CDC መግለጫን አይሙሉ።

 

የመንግስት የማስወጣት ጥበቃዎች ከአሁን በኋላ ንቁ አይደሉም። 

የዋሽንግተን ግዛት የማፈናቀል እገዳ ጁን 30፣ 2021 አብቅቷል። ከዚህ በኋላ ገዥው “ድልድይ” የሚባል ጊዜያዊ ሕግ (አዋጅ) አውጥቷል። ይህ የ“ድልድይ” አዋጅ አንዳንድ ግዛት አቀፍ ከቤት ማስወጣት ጥበቃዎችን ሰጥቷል። ነገር ግን እነዚህ ጥበቃዎች ኦክቶበር 31 2021 አብቅተዋል።

የቤት ኪራይ ዕዳ ካለብዎት፣ ባለንብረቱ አሁንም ምክንያታዊ የዳግም መክፈያ ዕቅድ ሊሰጥዎ ይገባል። እና በ Eviction Resolution Pilot Program (ERPP) በኩል ለሽምግልና እድል ሊሰጡዎት ይገባል። ከቤት ማስወጣት ካጋጠምዎ፣ 1-855-657-8387 ይደውሉ። ወይም  የሚከተለውን ተጠቅመው በመስመር ላይ ያመልክቱ CLEAR*Online

ስለ ዳግም ክፍያ ዕቅዶች የበለጠ ለማወቅ፣ የናሙና ዕቅዶችን ይመልከቱ፣ እና እርስዎ በሚኖሩበት ቦታ ተጨማሪ የአካባቢ ጥበቃዎች ካሉ ይወቁ፣ ይህን ይመልከቱ Coronavirus (COVID-19): ቤት አከራዬ አሁን ሊያስወጣኝ ይችላል?

 

እስከ ጃንዋሪ 1፣ 2022 የዘገየ ክፍያዎች አይፈቀዱም። 

አከራዮች ከማርች 1፣ 2020 እስከ ዲሴምበር 31፣ 2021 ድረስ በማንኛውም ጊዜ ኪራይ ለሚከፍሉ ተከራዮች ዘግይተው ክፍያ እንዲከፍሉ አይፈቀድላቸውም። 

 

 

Last Review and Update: Nov 02, 2021
Was this information helpful?
Back to top